በቪክቶሪያ ውስጥ ወንጀል ለደረሰባቸው አገልግሎቶች (Services for victims of crime in Victoria - Amharic)

የቪክቶሪያ መንግሥት ወንጀል ለደረሰባቸው እርዳታ መስመር በኩል ለርስዎና ቤተሰብዎ ያለክፍያ በነጻ መረጃ፤ ምክርና ድጋፍ ያቀርባል።

ወንጀል ለደረሰበት እርዳታ መስመር

የሚከፈት: ከጥዋቱ ሰዓት 8am እስከ ምሽት 11pm፤ በሳምንት 7 ቀናት
ለመደወል: 1800 819 817
ተክስት ለመላክ: 0427 767 891
ኢሜል: vsa@justice.vic.gov.au

በእርዳታ መስመር መደወል፤ ተክስት መልእክት ወይም ኢሜል የሚደረገው:

  • እንዴት ወንጀልን ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ እንደሚቻል ለማወቅ
  • እርስዎን ሊረዳ የሚችል ሌላ አገልግሎቶችን ለማግኘት
  • እንዴት የቪክቶሪያ ፍትሃዊ አሰራር ዘዴ እንደሚሰራ መረጃ ለማግኘት
  • በፍርድ ቤት ላይ ምስክርነትን ለመስጠት ከፈለጉ እርዳታ ለማግኘት
  • የሚፈቀድልዎት ከሆነ - ለመካካሻ ክፍያና ገንዘባዊ ድጋፍ ለማመልከት እርዳታ ለማግኘት
  • የርስዎንና የቤተሰብዎን ደህንነት ለመጠበቅ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለማወቅ ነው።

በአሁን ጊዜ በአደጋ ላይ ከሆኑ፤ ለፖሊስ በሶስት ዜሮ (000) አድርጎ መደወል። እንዲሁም ወደ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ ይችላሉ።

ሰዎችን በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ እንረዳለን

በየዓመቱ በሽዎች ለሚቆጠሩ የተለያየ እድሜ፤ ጾታዎች ላላቸው እና ከተለያየ ቦታ ለመጡ ሰዎች የወንጀል ሰለባ ሲደርስባቸው እንረዳለን።

ወንጀሉን ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ባይፈልጉም መርዳት እንችላለን

ስለ ወንጀል ለፖሊስ ለመንገር ጥሩ ምክንያቶች እንዳሉ ነው። የርስዎን ሪፖርት በጥልቀት በመውሰድ ወንጀሉን የፈጸመ ሰው ለማግኘት ይጥራሉ። እንዲሁም ለርስዎ መከላከል ይችላሉ።

ሪፖርቱን ለማቅረብ ዝግጁ ካልሆኑ ወይም ከፖሊስ ጋር ስለመነጋገሩ የሚያሳስብዎት ከሆነ የእርዳታ መስመር:

  • እርስዎን በማነጋገር ያለዎትን ሁኔታ ይረዳል
  • እርስዎን ሊረዱ የሚችሉ አገልግሎቶች መፈለግ፤ ምንም እንኳን ወንጀሉን ሪፖርት ማድረግ ባይፈልጉም
  • ከፈለጉ ለፖሊስ እንዲያነጋግሩ ይረዳል።

አስተርጓሚ መጠቀም ይችላሉ

አስተርጓሚ ከፈለጉ፤ የእርዳታ መስመር ያለክፍያ በነጻ አስተርጓሚ ያቀርብልዎታል። እንዲሁም ለርስዎ አስተርጓሚ ለማግኘት የሆነ ሰው ወደ እርዳታ መስመር እንዲደውልልዎት መጠየቅ ይችላሉ።

አስተርጓሚ ለማግኘት:

  1. ለእርዳታ መስመር በስልክ 1800 819 817 መደወል
  2. የርስዎን ስም፤ ስልክ ቁጥር እና ቋንቋ ለእነሱ መንገር
  3. አስተርጓሚ መልሶ ይደውልልዎታል።

አስተርጓሚ በሚደውልበት ጊዜ፤ በሞባይ ስልክ ላይ የሚታየው 'private number'፤ 'blocked' ወይም 'no caller ID' ሊሆን ይችላል።

Services for victims of crime in Victoria - information in Amharic (አማርኛ)
PDF 161.33 KB
(opens in a new window)

Updated